ለኢቢሲ ስፖርት ሽልማት ከአካዳሚው አራት ተጫዋቾችና አንድ አሰልጣኝ በእጩነት ተመረጡ

ለኢቢሲ ስፖርት ሽልማት ከአካዳሚው አራት ተጫዋቾችና አንድ አሰልጣኝ በእጩነት ተመረጡ(news 14)
በየአመቱ በስፖርት በተለያዩ ዘርፎች የኢቢሲ ስፖርት ሽልማት በማለት እውቅና የሚሰጠው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የ2013 እጩዎች በማለት ይፋ ካደረጋቸው መካከል የአካዳሚውን የአራት አመት ስልጠና በተለያየ ጊዜ በማጠናቀቅ ክለብ ከተቀላቀሉት ውስጥ አራት ነባር ሰልጣኞች እና አንድ አሰልጣኝን ይፋ አድረጓል፡፡
በዚሁ መሰረት የአለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን የግሏ ማድረግ የቻለችው ያለምዘርፍ የኋላው ( AW0)፣በ3‚000ሜትር መሰናክል እና በ5‚000 ሜትር ርቀቶች በተለያየ ጊዜ ውጤታማ መሆን የቻለው እንዲሁም በቶኪዮ 2020 በ3‚000 ሜትር መሰናክል የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆነው ጌትነት ዋለ (AM1)፣ለኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በመጫወት ተተኪነቷን ያስመሰከረች እና ከዚህ ቀደምም በኢቢሲ ስፖርት ሽልማት እጩ የነበረችው አረጋሽ ካልሳ (FW5) እና በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን ፕሪሚየር ሊግ ኮኮብ ጎል አግቢ ሆና ያጠናቀቀችው እና በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ የሴቶች ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በመጫወት ላይ የምትገኘው ንግስት በቀለ (FW5) ከነባር ሰልጣኞች ሲገኙበት ከአሰልጣኞች ደግሞ በኢትዮጵያ የ3‚000 ሜትር መሰናክል በርካታ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶችን በማፍራት የራሱን አሻራ ያስቀመጠው እና በቶኪዮ 2020 እና ከዚህ በፊት በነበሩ ኦሎምፒያዶች ዋና አሰልጣኝ የነበረው የአካዳሚው አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ (AC2) በመሆን በእጩነት ተመርጠዋል።
እጩ ተመራጮች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን የስፖርት ቤተሰቦች እጩዎቹ የልፋታቸውን ዋጋ ያገኙ ዘንድ 800 ላይ ከላይ ከስማቸው ጎን ያሰቀመጥነውን መለያ በማስገባት ድምፅ እንድትሆኗቸው እናሳውቃለን ።