Skip to main content

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቀቀ

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሰራተኞች እና የበላይ አመራሮች መስከረም 14 ቀን 2014 . የአካዳሚው የበላይ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ 1064/2010፤በፌደራል መንግስት ሰራተኞች ምልመላ እና መረጣ አፈፃፀም መመሪያ በዲሲፒሊን እና የቅሬታ አቀራረብ ስርኣት ደንብ ቁጥር 77/94 እንዲሁም በጀንደር ሜንስትሪሚንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስልጠናው በጀንደር ሜንስትሪሚንግ ላይ በአቶ ጫንያለው ዳኜ በስፖርት ኮሚሽን የወጣቶች ጉዳይ ባለሙያ እንዲሁም በዲሲፒሊን እና የቅሬታ አቀራረብ ስርኣት ደንብ ቁጥር 77/94 ላይ በወ/ ሻሼ ያዴሳ የአካዳሚው የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አማካኝነት ሰነዶች ቀርበው ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡

በቀረቡት ሰነዶች ላይ በመመስረት ከስልጠናው ተሳታፊዎች አስተያየቶች እንዲሁም በአሰራር ወቅት የሚታዩ የአዋጅ፣መመሪያዎች እና ደንቦች ጥሰቶች ላይ እና የአፈፃፀም ክፍተቶች ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት ማብራረያ እንዲሰጥባቸው የተጠየቀ ሲሆን በዚሁ መሰረት የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የአካዳሚው የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ መኮንን አማካኝነት በተሰጡ አሰተያየቶች እና ጥያቄዎች ላይ በመመስረት ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ተደርጎ በአካዳሚው የአስተዳደር ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ መኩሪያ አማካኝነት የማጠቃለያ ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡